2 ዜና መዋዕል 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎች፥ ማንቈርቈሪያዎች፥ ጥናዎችና የእሳት መጫሪያዎች፤ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ናቸው፤ የቤተ መቅደሱ የውጪ በሮችና የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉጠቶቹንም ድስቶቹንም ሙዳዮቹንም ጀሞዎቹንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። የውስጠኛውም ቤት የቅድስተ ቅዱሳን ደጆች የቤተ መቅደሱም ደጆች የወርቅ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕጠቶቹንም ድስቶቹንም ጭልፋዎቹንም ማንደጃዎቹንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ። የውስጠኛውም ቤት የቅድስተ ቅዱሳን ደጆች የቤተ መቅደሱም ደጆች የወርቅ ነበሩ። |
ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም።
እነርሱም ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችን፥ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደሱ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ።
ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የተለዩ ያደረጋቸውን ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎችን ዕቃዎች ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት አኖራቸው።
ዐመድ የሚጠራቀምባቸውን ድስቶችን፥ የእሳት መጫሪያዎችን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን አዘጋጅ፤ ሁሉም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።
ድስቶችን መሠዊያውን የሚያጸዱበትን የአካፋ ቅርጽ ያለውን መጫሪያውንና የዐመድ ማጠራቀሚያዎቹን ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ጭልፋዎችንና ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ከነሐስ የተሠሩ ሌሎችንም ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ወሰዱ።
እያንዳንዱ መዝጊያ ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት፤ ይህም ማለት ለያንዳንዱ መዝጊያ በመግፋት ወይም በመሳብ በሁለት በኩል የሚከፈቱ ሁለት ሳንቃዎች ማለት ነው።