የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበደ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር።
2 ዜና መዋዕል 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጌጦች፥ ቀንዲሎችና መኰስተሪያዎች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወርቅ የተቀረጹ አበባዎችን እና ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መኰስተሪያዎችን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበባዎቹንና ቀንዲሎቹን መኮስተሪያዎቹንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመብራቶች መቅረዞችንና በላያቸው ያሉ መብራቶችን፥ ጽዋዎቹን፥ ማንኪያዎቹን፥ ሥራ የሚሠሩባቸው ጻሕሎችንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበባዎቹንና ቀንዲሎቹን መኮስተሪያዎቹንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ። |
የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበደ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር።
የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎች፥ ማንቈርቈሪያዎች፥ ጥናዎችና የእሳት መጫሪያዎች፤ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ናቸው፤ የቤተ መቅደሱ የውጪ በሮችና የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ።
የሁሉም ጀርባቸው ወደ ውስጥ ነበር። የገንዳው ጐኖች ውፍረት ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ሲሆን፥ ክፈፉም እንደ ኩባያ ክፈፍ ሆኖ እንደ አሸንድዬ አበባ ወደ ውጪ የተቀለበሰ ነው፤ በርሜሉ ሥልሳ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።