የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።
2 ዜና መዋዕል 32:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል ብዙ ነገሮችን ካከናወነ በኋላ፥ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ፤ እንደሚያሸንፍ ተማምኖ የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስ እንዲህ ባለ ታማኝነት ነገሮችን ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ይሁዳን ወረረ። ድል አድርጎ የራሱ ሊያደርጋቸው በማሰብም የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ነገርና በታማኝነት ከተደረገው ነገር በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፥ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፥ የራሱም ሊያደርጋቸው አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህም ነገሮችና ከዚህ እውነት በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፤ ሊወስዳቸውም አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ነገርና ከዚህ እምነት በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፤ ሊወስዳቸውም አሰበ። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ ሌሎቹ ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ንጉሥ ኢዮስያስ ለቤተ መቅደሱ ይህን ሁሉ ካደራጀ በኋላ፥ የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው ካርከሚሽ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ አደጋ ለመጣል ሠራዊቱን አሰልፎ መጣ፤ ኢዮስያስም ሊቋቋመው ተነሣ፤
መንገዱን በርግዶ በሚከፍትላቸው መሪ አማካይነት በተከፈተው ሰፊ በር ተግተልትለው ይወጣሉ፤ እግዚአብሔርም ንጉሣቸው በፊታቸው እየሄደ ይመራቸዋል።