የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።
2 ዜና መዋዕል 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን እጅግ ውብ በሆነ የከበረ ድንጋይና ከፋርዋይም አገር በመጣ ወርቅ አስጊጦት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ መቅደሱን በከበረ ድንጋይ አስጌጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ የፈርዋይም ወርቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱንም በዕንቁ አስጌጠው፤ ወርቁም የፈርዋይም ወርቅ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱንም በከበረና በተመረጠ ዕንቍ፥ በወርቅም አስጌጠው፤ ወርቁም የፋሩሔም ወርቅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቱንም በዕንቍ አስጌጠው፤ ወርቁም የፈርዋይም ወርቅ ነበረ። |
የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።
የከበረ ድንጋይ የነበራቸው ሁሉ የሌዋዊው የጌርሾን ጐሣ አባል የሆነው ይሒኤል ለሚያስተዳድረው ለቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት በስጦታ ስም አቀረቡ፤
የቤተ መቅደሱን ግድግዳዎች፥ የጣራውን ክፈፎች፥ መቃኖችና መዝጊያዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስሎች ቀረጸባቸው።