La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 3:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለቅድስተ ቅዱሳኑ ከበፍታና ከሌላም ዐይነት ጨርቅ የተሠራ መጋረጃ ተደርጎለት ነበር፤ የመጋረጃውም ቀለም ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ሲሆን በላዩም ላይ የኪሩቤል ምስሎች ተቀርጸውበት ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከደማቅ ቀይ ፈትልና ከቀጭን በፍታ መጋረጃ ሠርቶ፣ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ ጠለፈበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰሎሞንም ከሰማያዊው ከሐምራዊውም ከቀዩም ሐር ከጥሩም በፍታ መጋረጃውን ሠራ፥ ኪሩቤልንም ጠለፈበት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሰ​ማ​ያ​ዊ​ውም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊ​ውም፥ ከቀ​ዩም ሐር፥ ከጥ​ሩም በፍታ መጋ​ረ​ጃ​ውን ሠራ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም ጠለ​ፈ​በት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሰማያዊውም ከሐምራዊውም ከቀዩም ሐር ከጥሩም በፍታ መጋረጃውን ሠራ፤ ኪሩቤልንም ጠለፈበት።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 3:14
7 Referencias Cruzadas  

ወደ ድንኳኑ የሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ በፍታ ተፈትሎ በእጅ ጥበብ ካጌጠ ቀጭን ሐር የተሠራ ነበር፤ እርሱም እንደ ድንኳኑ በር መግቢያ መጋረጃዎች ሁሉ ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር ቁመቱም ሁለት ሜትር ነበር፤


“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።


በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ፤ ምድርም ተናወጠች፤ አለቶችም ተሰነጠቁ፤


የምንገባውም በመጋረጃው፥ ማለትም በሥጋው አማካይነት በከፈተልን በአዲሱና ሕያው በሆነው መንገድ ነው።


ከሁለተኛው መጋረጃ በስተኋላ የምትገኘው ውስጠኛዋ ክፍል “ቅድስተ ቅዱሳን” ትባል ነበር።