ኢዮሣፍጥ አባቱ በዘመነ መንግሥቱ መጀመሪያ ላይ የነበረውን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት ስለ ተከተለና ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ጣዖት ስላላመለከ እግዚአብሔር ባረከው፤
2 ዜና መዋዕል 27:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን ስለ አቀና ገናና እየሆነ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአታምም በአምላኩ በጌታ ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። |
ኢዮሣፍጥ አባቱ በዘመነ መንግሥቱ መጀመሪያ ላይ የነበረውን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት ስለ ተከተለና ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ጣዖት ስላላመለከ እግዚአብሔር ባረከው፤
ኢዮሣፍጥ የአባቱን አምላክ የእግዚአብሔርን መመሪያ ተከተለ፤ ትእዛዞቹንም ጠበቀ፤ የእስራኤል ነገሥታት ያደርጉት የነበረውንም ዐይነት ክፉ ሥራ ከቶ አልፈጸመም፤
ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”
መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
በዐሞን ንጉሥና በሠራዊቱ ላይ ጦርነት ከፍቶ ድል አድርጎአቸው ነበር፤ ዐሞናውያንንም በየዓመቱ ለሦስት ዓመት በተከታታይ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብር፥ አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ስንዴና እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ገብስ እንዲገብሩለት አስገደዳቸው።