2 ዜና መዋዕል 26:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሞናውያንም ለዖዝያ ገበሩለት፤ እጅግ እየገነነ በመሄዱ ዝናው እስከ ግብጽ ድረስ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናውያን ለዖዝያን ግብር ገበሩለት፤ ኀይሉ ስለ ገነነም ዝናው እስከ ግብጽ ዳርቻ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ ተሰማ። |
ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት ሞአባውያንን ድል አደረገ፤ እስረኞቹ በመሬት ላይ እንዲጋደሙ አድርጎ ከየሦስቱ ሰዎች ሁለት ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ አደረገ። ስለዚህም ሞአባውያን የእርሱ ተገዢዎች በመሆን ይገብሩለት ነበር።
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፤
ከፍልስጥኤማውያን አንዳንዶቹ ብዙ ብርና ሌላም ዐይነት ስጦታ ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሲያበረክቱ፥ አንዳንድ ዐረቦች ደግሞ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ፍየሎች አመጡለት፤
በዐሞን ንጉሥና በሠራዊቱ ላይ ጦርነት ከፍቶ ድል አድርጎአቸው ነበር፤ ዐሞናውያንንም በየዓመቱ ለሦስት ዓመት በተከታታይ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብር፥ አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ስንዴና እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ገብስ እንዲገብሩለት አስገደዳቸው።
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ከዚህም በኋላ የሎጥ ዘሮች ወደሚኖሩበት ወደ ዐሞናውያን ምድር ትቃረባላችሁ፤ እነርሱንም አታስቸግሩአቸው፤ ወይም ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ ለእነርሱ ከሰጠኋት ምድር ለእናንተ ምንም አልሰጣችሁም።’ ”
ከአንድ ወር በኋላ የዐሞን ንጉሥ ናዖስ በገለዓድ ግዛት በምትገኘው በያቤሽ ከተማ ላይ ሠራዊቱን በማዝመት ከበባት፤ የያቤሽም ሰዎች ናዖስን “ከእኛ ጋር የውል ስምምነት አድርግ፤ እኛም የአንተ አገልጋዮች እንሆናለን” አሉት።