2 ዜና መዋዕል 25:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥቱን እንዳጠናከረ ወዲያውኑ አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሙሉ በሞት ቀጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንግሥቱም ከጸናለት በኋላ፣ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ሹማምት ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንግሥትም በጸናለት ጊዜ ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባርያዎች ገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንግሥትም በእጁ በጸናለት ጊዜ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ባሪያዎች ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንግሥትም በጸናለት ጊዜ አባቱን የገደሉትን ባሪያዎች ገደለ። |
ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ልጆቻቸውንም ያልገደለበት ምክንያት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ሕግ “ወላጆች ልጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል፥ ልጆችም ወላጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል በሞት አይቀጡም፤ አንድ ሰው በሞት መቀጣት ያለበት ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ ነው” ሲል የተናገረውን ቃል በማክበር ነው።