ኢዮአብ ግን “ንጉሥ ሆይ! አምላክህ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ፤ ይህንንም ሲያደርግ ለማየት እንድትበቃ ዕድሜህን ያርዝምልህ፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! ይህን ለማድረግ ስለምን ፈለግኽ?” አለው፤
2 ዜና መዋዕል 24:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሥ ኢዮአስ የሌዋውያኑን መሪ ዮዳሄን ጠርቶ፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ፥ እግዚአብሔር ለሚመለክበት ድንኳን አገልግሎት የሚሆን ግብር የእስራኤል ሕዝብ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ሌዋውያኑ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ሰብስበው ያመጡ ዘንድ ስለምን አላተጋሃቸውም?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ንጉሡ ሊቀ ካህኑን ዮዳሄን ጠርቶ፣ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና የእስራኤል ጉባኤ ለምስክሩ ድንኳን እንዲወጣ የወሰኑትን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያመጡ ሌዋውያኑን ያላተጋሃቸው ለምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም አለቃውን ዮዳሄን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የጌታ ባርያ ሙሴ ስለ ምስክሩ ድንኳን የእስራኤል ጉባኤ እንዲያወጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ላይ ሌዋውያን እንዲሰበስቡ ለምን አላተጋሃቸውም?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ኢዮአስም አለቃውን ኢዮአዳን ጠርቶ፥ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እስራኤልን በምስክሩ ድንኳን በሰበሰበ ጊዜ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋውያንን አልተከታተልህም?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም አለቃውን ዮዳሄን ጠርቶ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ስለ ምስክሩ ድንኳን የእስራኤል ጉባኤ እንዲያወጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋውያንን አላተጋሃቸውም?” አለ። |
ኢዮአብ ግን “ንጉሥ ሆይ! አምላክህ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ፤ ይህንንም ሲያደርግ ለማየት እንድትበቃ ዕድሜህን ያርዝምልህ፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! ይህን ለማድረግ ስለምን ፈለግኽ?” አለው፤
ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በመላው ኢየሩሳሌምና በይሁዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስራኤል ሕዝብ እንዲሰበሰብ ያዘዘውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ ትእዛዝ አስተላለፉ፤
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።
አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤