ስለዚህ ሰዎቹም በቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መስገድ ትተው፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራ ሴት አምላክ ጣዖቶችና ምስሎች መስገድ ጀመሩ። ይህንንም ኃጢአት በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።
2 ዜና መዋዕል 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአስ ከነገሠ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቤተ መቅደሱን ለማደስ ወሰነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢዮአስ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማደስ ወሰነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዮአስ የጌታን ቤት ለማደስ አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ኢዮአስ የእግዚአብሔርን ቤት ይጠግን ዘንድ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ ኢዮአስ የእግዚአብሔርን ቤት ይጠግን ዘንድ አሰበ። |
ስለዚህ ሰዎቹም በቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መስገድ ትተው፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራ ሴት አምላክ ጣዖቶችና ምስሎች መስገድ ጀመሩ። ይህንንም ኃጢአት በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።
የዚያች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ ክፉይቱ ሴት ተከታዮች ቤተ መቅደሱን አበላሽተውት ነበር፤ ንዋያተ ቅድሳቱን እንኳ ሳይቀር ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት በሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ይጠቀሙባቸው ነበር።