በብርቱም ቈስሎ ነበር፤ የጠላት ሠራዊት ከዚያ ተነሥቶ ከሄደ በኋላ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል በንጉሡ ላይ አሢረው በአልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት፤ ንጉሡም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።
2 ዜና መዋዕል 24:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሡ ላይ ያሤሩትም ሺምዓት ተብላ የምትጠራ የዐሞን ተወላጅ ልጅ የሆነው ዛባድና ሺምሪት ተብላ የምትጠራ የሞአብ ተወላጅ ልጅ የሆነው ይሆዛባድ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱ ላይ ያሤሩትም የአሞናዊቱ የሰምዓት ልጅ ዛባድና የሞዓባዊቱ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያሴሩበትም የአሞናዊቱ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቱም የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገደሉትም የአሞናዊቱ የሰማት ልጅ ዘቡድ፥ የሞዓባዊቱም የሰማሪት ልጅ ኢዮዛብድ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተማማሉበትም የአሞናዊቱ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቱም የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ። |
በብርቱም ቈስሎ ነበር፤ የጠላት ሠራዊት ከዚያ ተነሥቶ ከሄደ በኋላ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል በንጉሡ ላይ አሢረው በአልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት፤ ንጉሡም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።
የኢዮአስ ልጆች ታሪክ፥ በኢዮአስ ላይ ተነግረው የነበሩት የትንቢት ቃላትና ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንዳደሰ በነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ መግለጫ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።