እግዚአብሔር እንደገና በእስራኤል ላይ ስለ ተቈጣ በዳዊት አማካይነት መከራ እንዲመጣባቸው አደረገ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን “ሄደህ የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ቊጠር!” አለው፤
2 ዜና መዋዕል 24:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰዎቹም በቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መስገድ ትተው፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራ ሴት አምላክ ጣዖቶችና ምስሎች መስገድ ጀመሩ። ይህንንም ኃጢአት በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ትተው፣ የአሼራን ዐምዶችና ጣዖታትን አመለኩ፤ በበደላቸውም ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶቻቸውንም አምላክ ጌታን ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻቸውንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው ባዕድ አምላክንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚያም ወራት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን ትተው የማምለኪያ ዐጸዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ። |
እግዚአብሔር እንደገና በእስራኤል ላይ ስለ ተቈጣ በዳዊት አማካይነት መከራ እንዲመጣባቸው አደረገ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን “ሄደህ የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ቊጠር!” አለው፤
ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤
ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቊጣዬን አነሣሥተሃል፤
ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት በማጓደላቸውም ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለበት።
የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤
ነገር ግን የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከተልክ፤ ልክ አክዓብና በእርሱ እግር የተተኩት ነገሥታት የእስራኤልን ሕዝብ በእግዚአብሔር እንዳይታመኑ እንዳደረጉት ሁሉ አንተም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዳይሆኑ አደረግህ፤ ከአንተ የተሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን እንኳ ሳይቀር ገደልካቸው፤
ይህም ድርጊት እግዚአብሔርን አስቈጣ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ አሜስያስ አንድ ነቢይ ላከ፤ ይህም ነቢይ አሜስያስን “የገዛ ሕዝባቸውን ከአንተ እጅ ለማዳን እንኳ ላልቻሉ ለባዕዳን አማልክት ስለምን ሰገድክ?” ሲል ጠየቀው።
እንዲህም አሉአቸው፦ “እነዚህን እስረኞች ወደዚህ አታምጡብን! ከዚህ ቀደም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላሳዘንን ቊጣው በእኛ ላይ ወርዶአል፤ አሁንም በበደል ላይ በደል እንድንፈጽም ትፈልጋላችሁን?”
በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ እናንተም እንደምታዩት በእነርሱ ላይ ፍርሀትንና ድንጋጤን አምጥቶባቸዋል፤ መዘባበቻም አድርጎአቸዋል።
ሕዝቅያስ ግን ልቡ በትዕቢት ተሞልቶ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ስላደረገለት ቸርነት ሁሉ ተገቢ ምስጋና አላቀረበም፤ ከዚህም የተነሣ በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝብ ብርቱ ሥቃይ ደረሰባቸው።
እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ ይህም ያደረጉት በደል ቊጣዬን አነሣሥቶአል፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተነሣሣው ቊጣዬም ይፈጸማል እንጂ አይበርድም፤
በመላ አገራችሁ፥ በኮረብቶችና በተራሮች ላይ እንዲሁም በታላላቅ ዛፎች ሥር ሕዝቡ በየትውልዱ መሠዊያዎችንና የተለዩ ዐምዶችን አቁሞ አሼራ ተብላ ለምትጠራው ጣዖት ይሰግዳሉ።
ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።
የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ”
እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!
ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ።