2 ዜና መዋዕል 23:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተጠብቀው ይኖሩ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለጦር መኰንኖች ሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ዮዳሄ በአምላክ ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮች፣ ትላልቅና ትናንሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ዮዳሄ በጌታ ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ኢዮአዳ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ሰይፍና ጦር፥ አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። |
ሰይፋቸውን በእጃቸው ያያዙትን ጭፍሮች ሁሉ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን ተሰልፈው እንዲቆሙ አደረጋቸው።
ሌዋውያንና የይሁዳ ሕዝብ ካህኑ ዮዳሄ የሰጣቸውን መመሪያ ሁሉ ፈጸሙ፤ ዮዳሄም አገልግሎታቸውን ፈጽመው በሰንበት ቀን ከሥራ ነጻ መሆን የሚገባቸው ሌዋውያን አላሰናበታቸውም ነበር፤ ስለዚህ ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትና ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት እዚያው ስለ ነበሩ የጦር መኰንኖቹ በቂ ሰዎች ነበሩአቸው፤
አቤሜሌክም “በኤላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በእኔ ዘንድ አለ፤ እርሱም ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅሎ ተቀምጦአል፤ የምትፈልገው ከሆነ ውሰደው፤ በዚህ የሚገኝ የጦር መሣሪያ እርሱ ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም “እርሱኑ ስጠኝ! ከእርሱ የተሻለ ሰይፍ የትም አይገኝም” አለው።