ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት።
2 ዜና መዋዕል 22:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐረቦችና ተከታዮቻቸው ወረራ ባደረጉ ጊዜ በሰፈሩ ላይ አደጋ ጥለው ከሁሉ ታናሽ ከሆነው ከአካዝያስ በቀር የንጉሥ ኢዮራምን ወንዶች ልጆች በሙሉ ገደሉ፤ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ አካዝያስ በአባቱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐረቦች ጋራ ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም የነበሩት ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ወንድሞች ገድለዋቸው ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ። |
ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት።
በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኤልሳዕ ደቀ መዛሙርቱ ከሆኑት ነቢያት አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ራሞት ለመሄድ ተዘጋጅ፤ ይህንንም የዘይት ማሰሮ ያዝ፤
አካዝያስ ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ገዛ፤ የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ የሆነች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ እናቱ ወደ ክፋት የሚመራ ምክር ትሰጠው ስለ ነበር አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መጥፎ ምሳሌነት ተከተለ፤
ሁሉም በአንድነት በቤተ መቅደሱ ተሰብስበው ከንጉሡ ልጅ ከኢዮአስ ጋር የስምምነት ውል አደረጉ፤ ካህኑ ዮዳሄ እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር ለዳዊት ‘ልጆችህ ለዘለቄታ ይነግሣሉ’ ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት አሁን መንገሥ ያለበት ኢዮአስ ነው፤
ንጉሥ ዮአስም አሜስያስን ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ ከኤፍሬም ቅጽር በር አንሥቶ እስከ ማእዘን ቅጽር በር ድረስ ያለውን ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር ያኽል የሆነውን የኢየሩሳሌምን ቅጽር አፈረሰ።