ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
2 ዜና መዋዕል 21:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮራም መንግሥቱን ካጠናከረ በኋላ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም አንዳንድ የእስራኤል ባለሥልጣኖችን ገደለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞቹን በሙሉ ከጥቂት የእስራኤል አለቆች ጋራ በሰይፍ ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ሥልጣን ይዞ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ተነሥቶ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ፥ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ተነሥቶ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ። |
ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
ነገር ግን የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከተልክ፤ ልክ አክዓብና በእርሱ እግር የተተኩት ነገሥታት የእስራኤልን ሕዝብ በእግዚአብሔር እንዳይታመኑ እንዳደረጉት ሁሉ አንተም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዳይሆኑ አደረግህ፤ ከአንተ የተሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን እንኳ ሳይቀር ገደልካቸው፤
ስለዚህም ይሁዳን በመውረር ቤተ መንግሥቱን ዘረፉ፤ ከኢዮራም መጨረሻ ልጅ ከአካዝያስ በቀር የንጉሡን ሚስቶችና ወንዶች ልጆች ሁሉ እስረኞች አድርገው ወሰዱአቸው።
የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባሎች በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ አስተላለፈች።
ኢዩ በአክዓብ ሥርወ መንግሥት ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመፈጸም ላይ በነበረበት ጊዜ አካዝያስን አጅበው ከእርሱ ጋር መጥተው የነበሩትን የይሁዳ መሪዎችና የአካዝያስን ዘመዶች በዚያ አግኝቶ ሁሉንም ገደላቸው።
የሰይጣን ወገን እንደ ነበረውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል መሆን አይገባንም፤ እርሱ ወንድሙን ስለምን ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ ስለ ነበረና የወንድሙ ሥራ ግን ትክክል ስለ ነበረ ነው።
ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራም ሄዶ የጌዴዎን ልጆች የሆኑትን ሰባውን ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የጌዴዎን መጨረሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተደብቆ ስለ ነበር ከሞት ተረፈ፤