2 ዜና መዋዕል 20:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤) አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችም መጥተው ኢዮሣፍጥን፣ “ግዙፍ ሰራዊት ሊወጋህ ከሙት ባሕር ወዲያ ካለው ከኤዶም መጥቶብሃል፤ እነሆም፣ ሐሴሶን ታማር በተባለው በዓይንጋዲ ናቸው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎችም መጥተው እንዲህ በማለት ለኢዮሣፍጥ አወሩለት፦ “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዐይን-ጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ይገኛሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎችም መጥተው፥ “ከባሕሩ ማዶ ከሶርያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢዮሣፍጥ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወሬኞችም መጥተው “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢዮሳፍጥ ነገሩት። |
ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ።
ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።
“የደቡቡም ድንበር ከታማር ተነሥቶ እስከ መሪባ ቃዴስ ድረስ፥ ከዚያም ከግብጽ ሸለቆ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል፤ ይህም የደቡብ ድንበር ነው።
የጋድ ደቡባዊ ድንበር ከታማር ከተማ ደቡብ ተነሥቶ በመሪባ ቃዴስ እስከምትገኘው የውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤ ከዚያም የግብጽ ወሰን የሆነውን ወንዝ ተከትሎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል።
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።