ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ወይም በከተማይቱ ኗሪዎች መካከል የሚነሣውን ሕግ ነክ ክርክር በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይዳኙ ዘንድ ሌዋውያንን፥ ካህናትንና ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
2 ዜና መዋዕል 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ዳኞችን ሾሞአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱም ላይ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ዳኞችን ሾመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድሪቱም ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆች አኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆችን ሾመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆች አኖረ። |
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ወይም በከተማይቱ ኗሪዎች መካከል የሚነሣውን ሕግ ነክ ክርክር በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ ይዳኙ ዘንድ ሌዋውያንን፥ ካህናትንና ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን በኢየሩሳሌም ሾመ፤ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’