2 ዜና መዋዕል 18:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ ተብሎ የሚጠራ ሌላም ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል ስለማይናገር እርሱን አልወደውም” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “አንተ ይህን ማለት አይገባህም!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “መኖሩንማ በርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቀው አንድ ነቢይ አሁንም አለ፤ ነገር ግን ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት ተናግሮ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለ። ኢዮሣፍጥም፣ “ንጉሡ እንዲህ ማለት አይገባውም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ጌታን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው።” ኢዮሣፍጥም፦ “ንጉሡ እንዲህ አይበል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ክፉ እንጂ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለው። ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሡ እንዲህ አይበል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁል ግዜ ክፉ እንጅ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥም “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለው። |
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አዎ! አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ራስህን ለኃጢአት ሸጠሃል፤
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ አክዓብ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱን ጠርቶ “ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ” ሲል አዘዘው።
ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።
ከሕዝቡ መካከል አንዳንድ ሰዎች፦ “ኑ በኤርምያስ ላይ ዕቅድ እናውጣ! የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስተምሩ ካህናት፥ ምክር የሚሰጡ ጥበበኞች፥ የእግዚአብሔርን መልእክት የሚናገሩ ነቢያት ሁልጊዜ እናገኛለን፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ኤርምያስን ከማድመጥ ይልቅ በንግግሩ አጥምደን በወንጀል እንክሰሰው ተባባሉ።”
ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ሞት ይገባዋል፤ በእንደዚህ ያለ አነጋገር እየተናገረ በከተማይቱ የቀሩት ወታደሮች ወኔ እንዳይኖራቸው አድርጎአል፤ በከተማይቱ ሰው ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይኸው ነው፤ ሕዝቡን ለመጒዳት እንጂ ለመርዳት የሚፈልግ ሰው አይደለም።”
ንግግራቸውንም በመቀጠል! “የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? የእግዚአብሔር ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን?” ብለው ይጠይቃሉ፤ ለመሆኑ አካሄዳቸው ቀጥተኛ ለሆነ የእኔ ቃላት መልካም ነገር አያደርጉምን?
ስለዚህ ንጉሡ ወዲያውኑ አንዱን የዘብ ጠባቂ ወታደር የዮሐንስን ራስ ቈርጦ እንዲያመጣ ላከው፤ ወታደሩም ወደ ወህኒው ቤት ሄዶ የዮሐንስን ራስ ቈረጠ፤
ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ እኔንም አባቴንም ጠልተዋል።