2 ዜና መዋዕል 18:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስ “ሌሎች ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚክያስን ሊጠራ ሄዶ የነበረውም መልእክተኛ፣ “እነሆ፣ ሌሎቹ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው፣ ለንጉሡ መልካምን ነገር እየተነበዩ ነው፤ እባክህ የአንተም ቃል እንደ ቃላቸው ይሁን፤ ንጉሡን ደስ የሚያሠኘውን ተናገር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልክተኛ ሚክያስን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ ድምፅ ሆነው ለንጉሡ መልካም ነገር ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልእክተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካም ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልክተኛ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካም ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ” አለው። |
ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።