እግዚአብሔር በአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰሎሞንን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከዚህ በፊት እስራኤልን ከገዛ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ የተከበረ እንዲሆንም አደረገው።
2 ዜና መዋዕል 17:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮሣፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሳፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሳፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና የጎተራ ከተሞችን ሠራ። |
እግዚአብሔር በአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰሎሞንን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከዚህ በፊት እስራኤልን ከገዛ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ የተከበረ እንዲሆንም አደረገው።
ከፍልስጥኤማውያን አንዳንዶቹ ብዙ ብርና ሌላም ዐይነት ስጦታ ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሲያበረክቱ፥ አንዳንድ ዐረቦች ደግሞ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ፍየሎች አመጡለት፤
በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በሜዳዎች ላይ ብዙ የቀንድ ከብቶች ስለ ነበሩትም በገጠር የተመሸጉ መጠበቂያ ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጒድጓዶችንም ማሰ፤ ግብርና ይወድ ስለ ነበረ በኰረብታማ አገሮችና በለሙ ቦታ የወይን ተክል ተካዮችና ገበሬዎች ነበሩት።
ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።
ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።