እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥
2 ዜና መዋዕል 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኩ እግዚአብሔር ከንጉሥ አሳ ጋር መሆኑን ስላዩ፥ ከኤፍሬም፥ ከምናሴና ከስምዖን ነገዶች የሆኑ ብዙ ሰዎች ወደ አሳ መጥተው በግዛቱ ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ አሳም እነዚህን ሰዎች ሁሉ፥ እንዲሁም መላው የይሁዳና የብንያም ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኩ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ መሆኑን ባዩ ጊዜ፣ ከእስራኤል ብዙ ሰዎች እርሱን ተጠግተው ነበር፤ እርሱም ይሁዳንና ብንያምን እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነርሱ ጋራ የተቀመጡትን ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላኩም ከእርሱ ጋር እንደሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም፥ ከስምዖንም ፈልሰው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴ፥ ከስምዖንም መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ። |
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ዳዊት፥ ንጉሥ ሳኦልን ለመውጋት ከፍልስጥኤማውያን ጋር በዘመተ ጊዜ ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ወታደሮች ከዳዊት ጋር ለመተባበር ሄዱ፤ ሆኖም የፍልስጥኤማውያን መሪዎች “ዳዊት እኛን ከድቶ ወደ ቀድሞ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ብለው ስለ ፈሩ ከተመካከሩ በኋላ ወደ ቲግላግ እንዲመለስ አደረጉት፤
ከዚህም የተነሣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን በቅን መንፈስ ለማምለክ የፈለጉ ከመላው የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ብዙ ሰዎች ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ መኖሪያውን በኢየሩሳሌም ቢያደርግም እንኳ ሕዝቡ ወደ ቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ለማድረግ በደቡብ ከቤርሳቤህ ጀምሮ በሰሜን እስከ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ዳርቻ ድረስ እየተመላለሰ በየጊዜው በሕዝቡ መካከል ተገኝቶአል፤
ስለዚህ የይሁዳ ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሰሜን ግዛቶች የመጡ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ለዘለቄታው የሰፈሩ መጻተኞች ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።
“የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ።
በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።