በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
2 ዜና መዋዕል 13:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለይሁዳ ሕዝብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፥ ጌታም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። |
በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
አቢያና ሠራዊቱ እስራኤላውያንን ድል አድርገው ከፍ ያለ ጒዳት አደረሱባቸው፤ በዚህ ጦርነት ከእስራኤል አምስት መቶ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ተገደሉ።
ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ሠራዊት፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞች አልነበሩአቸውምን? ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ አንተ በእግዚአብሔር ስለ ታመንክ፥ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደረገህ።
በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
“ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካችን የባሳንን ንጉሥ ዖግንና ሕዝቡን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከእነርሱ አንድ እንኳ ሳናስቀር ሁሉንም አጠፋን።
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ።
እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም።
ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ።
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እስራኤላውያን በሠራዊቱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን በዚያ አገር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ወስደው የራሳቸው ርስት አደረጉት፤
ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቀዒላ መምጣቱ በተነገረው ጊዜ “እግዚአብሔር እርሱን በእጄ ሊጥልልኝ ነው፤ ዳዊት የግንብ ቅጽርና የተመሸጉ የቅጽር በሮች ወዳሉአት ከተማ በመዝለቁ ራሱን በወጥመድ ውስጥ አስገብቶአል” አለ።