2 ዜና መዋዕል 11:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቈየት ብሎም ሮብዓም፥ ማዕካ ተብላ የምትጠራውን የአቤሴሎምን ልጅ አግብቶ አቢያ፥ ዓታይ፥ ዚዛና ሼሎሚት ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያ፣ ዓታይ፣ ዚዛ፣ ሰሎሚት የተባሉትን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሷም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርስዋም አብያን፥ ኢያቲን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛንና ሰሎሚትን ወለደችለት። |
ሮብዓም በጠቅላላ ዐሥራ ስምንት ሚስቶችና ሥልሳ ቊባቶች ነበሩት፤ ከእነርሱም ኻያ ስምንት ወንዶችና ሥልሳ ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ከሚስቶቹና ከቊባቶቹ ሁሉ የአቤሴሎምን ልጅ ማዕካን አብልጦ ይወድ ነበር፤
መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሚካያ ተብላ የምትጠራ የጊብዓ ከተማ ተወላጅ የሆነ የኡሪኤል ልጅ ነበረች። በአቢያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ተነሥቶ ነበር፤