2 ዜና መዋዕል 10:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ውድቅ አድርጎ ሕዝቡን በማመናጨቅ መናገር ጀመረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ሮብዓምም በሽማግሌዎቹ የተሰጠውን ምክር ንቆ ሕዝቡን የሚያስከፋ መልስ ሰጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ |
ዮሴፍ ወንድሞቹን ባያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቊጣ ቃል “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እህል ለመሸመት ከከነዓን አገር መጣን” አሉት።
ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!” ሲል መለሰላቸው።