እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አባትህ ቀንበር አክዶብን ነበር፤ አንተ ግን አቅልልልን ለሚሉህ ሰዎች የምትሰጣቸው መልስ ይህ ነው፦ ‘የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች፤
2 ዜና መዋዕል 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ፤’ በላቸው፤” ብለው ተናገሩት። |
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አባትህ ቀንበር አክዶብን ነበር፤ አንተ ግን አቅልልልን ለሚሉህ ሰዎች የምትሰጣቸው መልስ ይህ ነው፦ ‘የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች፤
በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ከቶ ገለባ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን ቀድሞ የምትሠሩትን ያኽል ጡብ እየሠራችሁ ማስረከብ ይኖርባችኋል!” አላቸው።
እኔ በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እነርሱንም እንደ ርኩስ ቈጥሬ፥ ለአንቺ አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን ርኅራኄ አላደረግሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ሰዎች ላይ የጭቈና ቀንበር አበዛሽባቸው።
“እኔ የምደሰትበት ጾም የጭቈና ሰንሰለትና የፍትሕ መጓደል ቀንበር ታላሉ ዘንድ፥ ቀንበሩን ሰብራችሁ የተጨቈኑትን ነጻ ታወጡ ዘንድ አይደለምን?
እነርሱንም ቢሆን አምስት ወር ለማሠቃየት እንጂ ለመግደል ፈቃድ አልተሰጣቸውም፤ አንበጣዎቹ የደረሰባቸው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ያለ ነው።
ያ ዘመን በደረሰ ጊዜ የመረጣችሁት ንጉሥ ስለሚፈጽምባችሁ በደል በመረረ ሁኔታ ማጒረምረም ትጀምራላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን አቤቱታችሁን አያዳምጥም።”