2 ዜና መዋዕል 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን ካለበት፥ በገባዖን ከሚገኘው ኰረብታማ ማምለኪያ ስፍራ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ በእስራኤል ላይ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም የመገናኛው ድንኳን ካለበት ከገባዖን ኰረብታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም በገባዖን ካለው ከኮረብታው ስፍራ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም በገባዖን ካለው ኮረብታ ከምስክሩ ድንኳን ፊት ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም በገባዖን ካለው ከኮረብታው መስገጃ ከመገናኛው ድንኳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። |
ሰሎሞን በአንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና በዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች የተጠናከረ ሠራዊትን አደራጀ፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀረውን ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች በመመደብ በዚያው እንዲኖሩ አደረገ።
በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።