1 ተሰሎንቄ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኛ እንንቃ፤ ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እንንቃ፤ ራሳችንንም እንግዛ እንጂ እንደሚያንቀላፉት እንደ ሌሎቹ አንሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲያስ እንንቃ፥ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። |
“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
የመርከብ አዛዡም ወደ እርሱ ቀርቦ “እንዴት ትተኛለህ? ኧረ እባክህ ተነሥና ወደ አምላክህ ጸልይ፤ ምናልባት ራርቶልን ሕይወታችንን ያድን ይሆናል” አለው።
እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።
እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን።
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
እንዲሁም ሴቶች ጠጒርን በማሳመር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቊ ወይም ውድ በሆነ ልብስ በማጌጥ ሳይሆን በማፈርና በትሕትና ተገቢ የሆነ የጨዋ ልብስ ይልበሱ።
ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”