1 ተሰሎንቄ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል በሥራ የሚደክሙትን፥ በጌታ ኢየሱስ አለቆቻችሁንና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሩአቸው እንለምናችኋለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ መካከል በትጋት የሚሠሩትን፣ በጌታም የበላዮቻችሁና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም እንድታውቁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ! በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ። |
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
በጌታ አገልግሎት ለሚደክሙት ለትሩፋይናና ለትሩፎሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት እጅግ ለደከመችውና በክርስቶስ ለምወዳት ለፔርሲስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው በቤተ ክርስቲያን የተለያየ አገልግሎት እንዲኖረው አድርጓል፤ በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛ ነቢያትን፥ ሦስተኛ መምህራንን ሾሞአል። ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩትን ሰዎች መድቦአል።
ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤
ይህም የሚሆነው ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ሳታቋርጡ አጥብቃችሁ በመያዝ ነው፤ በዚህ ዐይነት ሩጫዬም ሆነ ሥራዬ ከንቱ ሆኖ ስለማይቀር ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የምመካበት ምክንያት ይኖረኛል ማለት ነው።
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።
አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት ያልተስተካከለውን እንድታስተካክልና ባዘዝኩህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን በየከተማው እንድትሾም ነው።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ኮከቦችና የሰባቱም የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ኮከቦች የሰባቱ አብያተ ክርስቲያን መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞችም ሰባት አብያተ ክርስቲያን ናቸው።”
“ለትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ የእሳት ነበልባል የሚመስሉ ዐይኖች ካሉትና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ካሉት፥ ከእግዚአብሔር ልጅ የተነገረ ነው፤
“ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ የመጀመሪያና የመጨረሻ ከሆነው፥ ሞቶ ከነበረውና ሕያው ከሆነው የተነገረ ነው፤
“ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ኮከቦች ከያዘው የተነገረ ነው፤ ሥራህን ዐውቃለሁ፤ በስም ሕያው ነህ፤ ነገር ግን ሞተሃል።
“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤
“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።