1 ተሰሎንቄ 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ራሱ በታላቅ ትእዛዝ፣ በመላእክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳልና። በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ራሱ በትእዛዝ ቃል በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ ክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ |
በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
በዚያም ዘመን ትልቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር ምድር ጠፍተው የነበሩትና ወደ ግብጽ ተሰደው የነበሩት እስራኤላውያንም ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በተቀደሰው ተራራ ላይ ይሰግዳሉ።
እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?
እንደ ተራራ በፊትህ የተደቀነው መሰናክል ሁሉ ይወገዳል፤ ቤተ መቅደሱንም መልሰህ ትሠራለህ፤ የመደምደሚያውንም ድንጋይ በስፍራው መልሰህ በምታኖርበት ጊዜ ሕዝቡ ‘እንዴት ውብ ነው! ውብ ነው!’ እያሉ የደስታ ድምፅ ያሰማሉ።”
እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ ይገለጣል፤ የእርሱም ፍላጻዎች እንደ መብረቅ ይወረወራሉ፤ እግዚአብሔር አምላክ የመለከት ድምፅ ያሰማል፤ ከደቡብ በኩል እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ ያልፋል።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
በእስራኤል ሕዝብ ላይ ክፉ አጋጣሚ ወይም ችግር እንደማይደርስባቸው ይታያል፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሥ መሆኑንም በይፋ ይናገራሉ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ እንዳልከው ነው፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታዩታላችሁ፤ እንዲሁም በሰማይ ደመና ሆኖ ሲመጣ ታዩታላችሁ እላችኋለሁ።”
“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
ይህም የሚሆነው ለእያንዳንዱ በየተራው ነው፤ ክርስቶስ ከሞት የመነሣት የመጀመሪያው ምሳሌ ነው፤ በኋላም ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የእርሱ የሆኑት ከሞት ይነሣሉ።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።
አሁን መከራን ለምትቀበሉትም ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል። ይህም የሚሆነው ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በሚወርድበት ጊዜ ነው፤
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያን ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ፍጥረት ሁሉ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል። ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል፤
የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ አስከሬን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ “ጌታ ይገሥጽህ” አለው እንጂ የስድብ ቃል አልተናገረም።
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህን ጻፍ፤ “ከእንግዲህ ወዲህ የጌታ ኢየሱስ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው!” መንፈስ ቅዱስም “አዎ! ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል” ይላል።
ከዚህ በኋላ ስመለከት አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት የእምቢልታቸውን ድምፅ በሚያሰሙበት ጊዜ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” እያለ ሲጮኽ ሰማሁ።