ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ፤ በልስጥራ ጢሞቴዎስ የሚባል አማኝ ይኖር ነበር፤ እናቱ አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበር።
1 ተሰሎንቄ 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእምነታችሁ እንዲያጸናችሁና እንዲያበረታችሁ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል ሥራ ከእኛ ጋራ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን፥ የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤ |
ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ፤ በልስጥራ ጢሞቴዎስ የሚባል አማኝ ይኖር ነበር፤ እናቱ አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበር።
ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ በመጡ ጊዜ ጳውሎስ “ኢየሱስ መሲሕ ነው” በማለት ለአይሁድ በትጋት እየመሰከረ በማስተማር ጊዜውን ሁሉ ያሳልፍ ነበር።
እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት።
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየቦታውና በየአብያተ ክርስቲያኑ እንደማስተምረው እርሱ እኔ በክርስቶስ ያገኘሁትን የአዲስ ሕይወት መመሪያ ያሳስባችኋል።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ፥
እኔና ሲላስ፥ ጢሞቴዎስም የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን የሰበክንላችሁ ሁልጊዜ “አዎን” በሚል ቃል ብቻ እንጂ፥ “አዎን ወይም አይደለም” በሚል አወላዋይ ቃል አልነበረም።
ስለ ቲቶ ማወቅ ቢያስፈልግ እናንተን ለመርዳት አብሮኝ የሚሠራ የሥራ ጓደኛዬ ነው፤ ከእርሱ ጋር ስለሚመጡት ስለ ሌሎች ወንድሞች የሆነ እንደ ሆነ እነርሱ የአብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ለክርስቶስ ክብር የቆሙ ናቸው።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።
ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነው የታመነውና የተወደደው ወንድም ኦኔሲሞስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱ በዚህ ስፍራ ስላለው ነገር ሁሉ ያስታውቋችኋል።
በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።