ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
1 ተሰሎንቄ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊትና ቀን በብርቱ የምንጸልየው በዐይነ ሥጋ እንድናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለመሙላት እንድንችል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና ልናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ ተግተን እንጸልያለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የጎደለውንም ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ አብዝተን እንጸልይ የለምን? |
ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው።
በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እያንዳንዱ ሰው በክርስቶስ ብቁ ሰው እንዲሆን አድርገን ለማቅረብ ለሰው ሁሉ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምከር ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።
ይህን በማሰብ ስለ እናንተ ሳናቋርጥ የምንጸልየው አምላካችን ለጥሪው ብቁዎች እንዲያደርጋችሁና መልካም ለማድረግ ያላችሁን ፈቃድና የእምነት ሥራችሁን ሁሉ በኀይሉ እንዲፈጽምላችሁ ነው።
አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች ነበሩአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ሌሊትና ቀን፦ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፥ የነበረ፥ ያለና የሚመጣውም” ከማለት አያቋርጡም ነበር።