በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
1 ነገሥት 8:63 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችንና መቶ ሃያ ሺህ በጎችን አቀረበ። ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፤ አከበሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ለደኅንነት መሥዋዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች አቀረበ። ንጉሡና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ። |
በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
አሁን እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመዘጋጀት ላይ ነኝ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እኔና ሕዝቤ በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን የምናጥንበት የተቀደሰውን ኅብስት ሳናቋርጥ ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት፥ በየቀኑ ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በሌሎችም በተቀደሱ በዓላት እግዚአብሔር አምላካችንን ለማክበር የሚቃጠለውን መሥዋዕት የምናቀርብበት የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፤ የእስራኤል ሕዝብ ይህን ለዘለዓለም እንዲያደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።
ንጉሥ ሕዝቅያስ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ሰባት ሺህ በጎችንና ፍየሎችን፥ ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ደግሞ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ዐሥር ሺህ በጎችንና ፍየሎችን ዐርደው እንዲበሉ ለሕዝቡ ሰጡ፤ ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤
ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር የምረቃ በዓል በተከበረበት ዕለት ሌዋውያኑ በጸናጽል፥ በበገናና በመሰንቆ በዓሉን እንዲያከብሩ ከየሚኖሩበት ስፍራ ተፈልገው መጡ።
ቀድሞ ኢየሩሳሌም በበዓል ቀን ለመሥዋዕት በሚቀርቡ በጎች ትሞላ እንደ ነበረች የፈራረሱት ከተሞች በሕዝብ የተሞሉ ይሆናሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።”
በሺህ የሚቈጠሩ አውራ በጎችን ወይም የዐሥር ሺህ ወንዞችን ውሃ የሚያኽል የወይራ ዘይት ባቀርብለት ይደሰት ይሆን? ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴ የበኲር ልጄን ልሠዋለትን?