1 ነገሥት 8:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መቼም ኀጢአት የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ በአንተ ላይ ኀጢአት ቢሠሩ፣ አንተም ተቈጥተህ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ እነርሱም ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ የጠላት ምድር ቢጋዙ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የማይበድልም ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ተቈጥተህም ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላቶች ሀገር ቢማረኩም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “የማይበድልም ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ተቆጥተህም ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላቶች አገር ቢማረኩም፥ |
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
“መቼም በደል የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ እስራኤላውያን ኃጢአት በመሥራት አንተን ቢያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ያ አገር ሩቅ ቢሆንም እንኳ፥
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።
“እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ።
እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’