ጸሎታቸውን ስማ፤ በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
1 ነገሥት 8:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይ በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር፣ ዋግ ወይም አረማሞ፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚከሠትበት ጊዜ፣ ወይም ከተሞቻቸውን ጠላት በሚከብብበት ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚደርስባቸው ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “በምድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ፥ ወይም አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥ |
ጸሎታቸውን ስማ፤ በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
“በምድርህ ላይ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን ወይም ሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህ ወይም እግዚአብሔር በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን በሰይፍ ከሚመታህና ቸነፈር በምድሪቱ ላይ አምጥቶ በእስራኤል ምድር ሁሉ በሞት የሚቀሥፍ መልአክ ከሚልክብህ የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር የማቀርበውን መልስ ስጠኝ።”
‘እኛን ለመቅጣት ጦርነትን፥ ቸነፈርን ወይም ራብን የመሳሰለውን መቅሠፍት ብታደርስብን የአንተ ስም ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት መጥተን በመቆም ከመከራችን እንድታድነን ወደ አንተ እንጸልያለን፤ አንተም ጸሎታችንን ሰምተህ በመታደግ ታድነናለህ’ ብሎ ነው።
ያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ከበባ ያደረገበት ጊዜ ነበር፤ እኔም በዚያን ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ነበር፤
ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ።
የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤