አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በምርኮ የሚገኙትንም ሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው።
1 ነገሥት 8:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝብህ እስራኤል በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት በጠላቶቻቸው ድል ሲሆኑ ተጸጽተውም ወደ አንተ በመመለስ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና የአንተን ይቅርታ ለማግኘት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትሕትና ቢለምኑህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሣ፣ በጠላቶቻቸው ድል በሚሆኑበት ጊዜ፣ ወደ አንተም ተመልሰው ስምህን ቢጠሩ፣ በዚህም ቤተ መቅደስ ወደ አንተ ቢጸልዩና ልመናቸውን ቢያቀርቡ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል ቢመቱ፥ ነገር ግን ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል ቢሆኑ፥ ወደ አንተም ቢመለሱ፥ ለስምህም ቢናዘዙ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል በተመቱ ጊዜ፥ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥ |
አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በምርኮ የሚገኙትንም ሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው።
ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፥ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፥
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።
እግዚአብሔር አስፈሪ በሆነው ቊጣና መዓቱ ሕዝቡን እንደሚቀጣ የተናገረ በመሆኑ ምናልባት በመጸጸት ከክፉ ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይለምኑት ይሆናል።”
ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማፍረሳችሁ እናንተን ለመቅጣት ጦርነት አመጣባችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ብትሰበሰቡም ሊፈወስ የማይችል በሽታ በመካከላችሁ እልካለሁ፤ ለጠላቶቻችሁም እጃችሁን ለመስጠት ትገደዳላችሁ።
እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎች ያደረጉትንና ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህም ራርቶላቸው በእነርሱ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቅጣት አልፈጸመም።
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤
ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለሚልካቸው ለጠላቶችህ አገልጋይ ትሆናለህ። በሁሉ ነገር በመቸገርም ትራባለህ፤ ትጠማለህ፤ ትታረዛለህ። ፈጽሞ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር አንተን በጠላቶችህ እንደ ብረት በጠነከረ የአገዛዝ ቀንበር በብርቱ እንድትጨቈን ያደርጋል።