የመንኰራኲሮቹም ቁመት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር፤ መንኰራኲሮቹም በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ነሐስ ሥር ነበሩ፤ የመንኰራኲሮችም ወስከምቶች ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤
1 ነገሥት 7:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንኰራኲሮቹም የሠረገላ መንኰራኲሮችን ይመስሉ ነበር፤ ወስከምቶቻቸው፥ ቅትርቶቻቸውና ዐቃፊዎቻቸው ሁሉም ከነሐስ ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንኰራኵሮቹ የሠረገላ መንኰራኵር መሰል ሲሆኑ፣ ወስከምቶቹ የመንኰራኵሮቹ ክፈፎችና ዐቃፊዎቻቸው እንዲሁም ወስከምቶቹ የሚገቡባቸው ቧንቧዎች በሙሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንኰራኲሮቹም የሠረገላ መንኰራኲሮችን ይመስሉ ነበር፤ ወስከምቶቻቸው፥ ቅትርቶቻቸውና ዐቃፊዎቻቸው ሁሉም ከነሐስ ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመንኰራኵሮቹም ሥራ እንደ ሰረገላ መንኰራኵር ሥራ ነበረ፤ ወስከምቶቹና የመንኰራኵሮቹ ክፈፍ፥ ቅትርቶቹም፥ ወስከምቱ የሚገባበት ቧምቧ ሁሉ በምስል የፈሰሰ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመንኰራኵሮቹም ሥራ እንደ ሠረገላ መንኰራኵር ነበረ፤ ወስከምቶቹና የመንኰራኵሮቹ ክፈፍ ቅትርቶቹም ወስከምቱም የሚገባበት ቧምቧ ሁሉ በምስል የፈሰሰ ነበረ። |
የመንኰራኲሮቹም ቁመት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር፤ መንኰራኲሮቹም በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ነሐስ ሥር ነበሩ፤ የመንኰራኲሮችም ወስከምቶች ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤
የእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘኖች በየግርጌአቸው ከእነርሱው ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት መደገፊያዎች ነበሩአቸው።
አራቱም መንኰራኲሮች ተመሳሳይ ነበሩ፤ እያንዳንዱም እንደ ከበረ ዕንቊ ያንጸባርቅ ነበር፤ እንዲሁም እያንዳንዱ አንዱ መንኰራኲር በሌላው መንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፍ ይመስል ነበር።