የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን እግዚአብሔር ከመላው የእስራኤል ግዛት መካከል ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፤ የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።
1 ነገሥት 22:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም በሠላሳ አምስት ዓመት ዕድሜው ነግሦ ኻያ አምስት ዓመት በኢየሩሳሌም ገዛ፤ እናቱም ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በሠላሳ አምስት ዓመት ዕድሜው ነግሦ ኻያ አምስት ዓመት በኢየሩሳሌም ገዛ፤ እናቱም ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሣፍጥም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት ጎበዝ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ። እናቱም ዓዙባ የተባለች የሴሜይ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት ጎበዝ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ። እናቱም ዓዙባ የተባለች የሺልሒ ልጅ ነበረች። |
የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን እግዚአብሔር ከመላው የእስራኤል ግዛት መካከል ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፤ የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።
ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ሠራ፤ ይሁን እንጂ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፤
እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።
ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው በሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፤