ከዚያም በኋላ ሼሜር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያን ኰረብታ በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛ፤ ዖምሪ ኰረብታውን ከመሸገ በኋላ ከተማ ቈረቈረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሼሜር ስም “ሰማርያ” ብሎ ሰየማት።
1 ነገሥት 22:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አክዓብ በዚህ ዐይነት ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ስለ ሞተም ወደ ሰማርያ አምጥተውት እዚያው ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ አክዓብ በዚህ ዓይነት ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰማርያም መጡ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰማርያም መጡ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት። |
ከዚያም በኋላ ሼሜር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያን ኰረብታ በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛ፤ ዖምሪ ኰረብታውን ከመሸገ በኋላ ከተማ ቈረቈረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሼሜር ስም “ሰማርያ” ብሎ ሰየማት።
ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፤ ”
ፀሐይ ልትጠልቅ ጥቂት ሲቀራትም “እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ተመልሶ ይሂድ!” የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ።
የሐሰተኞች ነቢያትን ምልክቶችና፥ የሟርተኞችን ጥንቈላ ከንቱ አደርጋቸዋለሁ። የጥበበኞችን ዕውቀት እገለብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ወደ ሞኝነት እለውጠዋለሁ፤
ራእያቸው ሐሰት ነው፤ ሟርታቸውም ውሸት ነው፤ እግዚአብሔር ሳይልካቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ይላሉ፤ ይህም ሆኖ ቃላቸው ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ይገምታሉ።