እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ ናታንም ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ አንዱ ሀብታም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድኻ ነበር፤
1 ነገሥት 20:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያና ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ።” ንጉሡም “በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ታዲያ እኔ አገልጋይህ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ።’ ” የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ራስህ ፈርደሃል፤ ይኸው ይፈጸምብሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያና ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ።” ንጉሡም “በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል” አለው። |
እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ ናታንም ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ አንዱ ሀብታም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድኻ ነበር፤
እርስዋም እንዲህ አለችው፤ “በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ይህን የመሰለ በደል የፈጸምከው ስለምንድን ነው? ልጅህ ከተሰደደበት አገር ተመልሶ እንዲመጣ አልፈቀድክለትም፤ ስለዚህ አሁን በተናገርከው ቃል በራስህ ላይ ፈርደሃል፤
ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ፥ ነቢዩ ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ጥሬ ብር መቀጫ ትከፍላለህ’ አለኝ።
ቸል በማለት የእግዚአብሔርን ሥራ ከልብ የማይፈጽም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር በሚያዘውም ጊዜ ሰይፉን ከደም የሚከለክል የተረገመ ይሁን!
ጌታውም ‘አንተ መጥፎ አገልጋይ! በአነጋገርህ እፈርድብሃለሁ፤ እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የምሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆኔን ዐውቀሃል፤