የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ “ምታኝ!” አለው። ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት አልፈቀደም፤
1 ነገሥት 20:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ነቢዩ ወደ ሌላ ሰው ሄዶ “ምታኝ!” አለው፤ ያም ሰው “እሺ” በማለት በኀይል ደብድቦ አቈሰለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢዩም ሌላ ሰው አግኝቶ፣ “እባክህ ምታኝ” አለው። ስለዚህ ያ ሰው መትቶ አቈሰለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ነቢዩ ወደ ሌላ ሰው ሄዶ “ምታኝ!” አለው፤ ያም ሰው “እሺ” በማለት በኃይል ደብድቦ አቆሰለው። |
የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ “ምታኝ!” አለው። ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት አልፈቀደም፤
ስለዚህም ያ ነቢይ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።