ሮቤልም “እኔ በልጁ ላይ ጒዳት እንዳታደርሱ ነግሬአችሁ ነበር፤ ነገር ግን አልሰማችሁኝም፤ እነሆ፥ እርሱን በመግደላችን በቀሉን እየተቀበልን ነው” አላቸው።
1 ነገሥት 2:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደማቸውም ዕዳ ለዘላለም በኢዮአብና በዘሩ ራስ ላይ ይሁን። ነገር ግን በዳዊትና በዘሩ፣ በቤቱና በዙፋኑ ላይ የእግዚአብሔር ሰላም ለዘላለም ጸንቶ ይኑር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የጌታ ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደማቸውም በኢዮአብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘለዓለም ይመለስ፤ ለዳዊት ግን ለዘሩና ለቤቱ፥ ለዙፋኑም የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም ይሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደማቸውም በኢዮአብ ራስና በዘሩ ራስ ላይ ለዘላለም ይመለስ፤ ለዳዊት ግን ለዘሩና ለቤቱ ለዙፋኑም የእግዚአብሔር ሰላም ለዘላለም ይሁን።” |
ሮቤልም “እኔ በልጁ ላይ ጒዳት እንዳታደርሱ ነግሬአችሁ ነበር፤ ነገር ግን አልሰማችሁኝም፤ እነሆ፥ እርሱን በመግደላችን በቀሉን እየተቀበልን ነው” አላቸው።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።
ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
ስለዚህ በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የእኔን የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ቤተሰቤን ባርከኸዋል፤ እርሱም ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል።”
ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ በእኔ ስም የማለውን መሐላ ንቆ ቃል ኪዳኑን በማፍረሱ መሐላው በራሱ ላይ እንዲደርስ አደርጋለሁ።
ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።
ነገር ግን አይሁድ በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ የልብሱን ትቢያ አራግፎ “እንግዲህ ቢፈረድባችሁ በራሳችሁ ጥፋት ነው! እኔ ኀላፊነት የለብኝም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ!” አላቸው።
ይህም የሆነው ወንድማቸው አቤሜሌክ የገደላቸውን የጌዴዎንን ሰባ ልጆች ደምና እነርሱንም እንዲገድል ያበረታቱትን የሴኬምን ሰዎች ለመበቀል ነው።