አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤
1 ነገሥት 18:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛው ጊዜ አገልጋዩ፣ “እነሆ፤ የሰው እጅ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው” አለው። ኤልያስም፣ “ሂድና አክዓብን፣ ‘ዝናቡ ሳያግድህ፣ ሠረገላህን ጭነህ ውረድ’ ብለህ ንገረው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕር ውኃ ቋጥራ ስትወጣ አየሁ” አለ። እርሱም፥ “ወጥተህ አክዓብን፦ ዝናብ እንዳይዝህ ሰረገላህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ጊዜ “እነሆ፥ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጣች፤” አለ። እርሱም “ወጥተህ አክዓብን ‘ዝናብ እንዳይከለክልህ ሠረገላን ጭነህ ውረድ፤’ በለው፤” አለ። |
አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤
ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”
ደግሞም ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ደመና በስተ ምዕራብ በኩል ስታዩ ወዲያውኑ፦ ‘እነሆ! ዛሬ ሊዘንብ ነው!’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይዘንባል።
እነርሱም እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላ በታሰረበት ቀንበር ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሰው ዘጉባቸው።
ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤