ከዚህም የተነሣ ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በመኰብለል አመለጠ፤ ሰሎሞንም እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቈየ።
1 ነገሥት 14:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት፣ የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሮብዓምም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮብዓምም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ መጣ። |
ከዚህም የተነሣ ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በመኰብለል አመለጠ፤ ሰሎሞንም እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቈየ።
ስለዚህ ንጉሥ ሺሻቅ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ፥ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ፥ ንጉሥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤