1 ነገሥት 14:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ሁሉ በማዘን አልቅሰው ይቀብሩታል፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተደሰተበት ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ ከኢዮርብዓምም ቤተሰብ መካከል ሥርዓተ ቀብር በሚገባ የሚፈጸምለት እርሱ ብቻ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ መልካም ነገር ያገኘበት እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ በወግ በማዕርግ የሚቀበር እርሱ ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ሁሉ በማዘን አልቅሰው ይቀብሩታል፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የተደሰተበት ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ ከኢዮርብዓምም ቤተሰብ መካከል ሥርዓተ ቀብር በሚገባ የሚፈጸምለት እርሱ ብቻ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደንገጡሮችሽም ሊቀበሉሽ ይወጣሉ፤ ልጅሽም ሞተ ይሉሻል፥ እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል። |
ንጉሥ ሮብዓም በደሉን አምኖ ራሱን ስላዋረደ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ሙሉ በሙሉ ጒዳት አላደረሰበትም፤ እንዲያውም በይሁዳ ሁሉ ነገር መልካም ሆነ።
ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ስለ ንጉሥ ኢዮስያስ አታልቅሱ፤ በመሞቱም አትዘኑ፤ ነገር ግን የኢዮስያስ ልጅ ሻሉም፤ ዳግመኛ ወደማይመለስበት ቦታ ስለሚወሰድ፥ የትውልድ አገሩንም ዳግመኛ ስለማያይ፥ ለእርሱ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም የሚለው ይህ ነው፥ “እርሱ በሚሞትበት ጊዜ ‘ዋይ! ወዮ! ወንድሜ ሆይ!’ እያሉ በማልቀስ አያዝኑለትም፤ እንዲሁም ‘ጌታዬ ሆይ! ንጉሤ ሆይ! ወዮ!’ እያለ የሚያለቅስለት አይኖርም።