1 ነገሥት 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማይቱ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ ገላጣ በሆነው ገጠር የሚሞቱትንም አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢዮርብዓም ወገን በከተማ የሞተውን ውሾች፣ በባላገር የሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል፤ እግዚአብሔር ተናግሯልና!’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማይቱ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ ገላጣ በሆነው ገጠር የሚሞቱትንም አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ጌታ ነኝ።’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ከኢዮርብዓም ወገን በከተማዪቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢዮርብዓምም ወገን በከተማይቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።’ |
ወዲያውኑም የኢዮርብዓምን ቤተሰብ አባላት ሁሉ መፍጀት ጀመረ፤ እግዚአብሔር የሴሎ ተወላጅ በሆነው በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ቤተሰብ በሙሉ ተገደሉ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።
እኔ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የምለው ይህ ነው ‘ናቡቴን መግደልህ አንሶህ ሀብቱንም ልትወርስበት ነውን?’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ እንዲሁም የአንተን ደም ይልሱታል!’ ”
የእስራኤል ነገሥታት በነበሩት በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓምና በአኪያል ልጅ በበዕሻ ቤተሰቦች ላይ ያደረግኹትን፥ ሁሉ በአክዓብ ቤተሰብ ላይ እፈጽማለሁ።
“ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።”
እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤