ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።
1 ነገሥት 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽማግሌውም “ወደ ቤቴ መጥተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ነቢዩ፣ “ዐብረን ወደ ቤት እንሂድና ምግብ ብላ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌውም “ወደ ቤቴ መጥተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ እንጀራም ብላ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፤ እንጀራም ብላ፤” አለው። |
ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።
ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤት መሄድም ሆነ ግብዣህን መቀበል አልችልም፤ በዚህም ከአንተ ጋር ምንም ዐይነት እህል ውሃ አልቀምስም፤