ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።
1 ነገሥት 12:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገው የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲመልሱ መላውን የይሁዳ ቤትና የብንያምን ነገድ ሰበሰበ፤ የሰራዊቱም ቍጥር አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገው የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቁጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሮብዓም ግን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእስራኤልንም ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሰሎሞን ልጅ ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳ ቤት ሁሉና ከብንያም ነገድ የተመረጡትን አንድ መቶ ሃያ ሺህ ተዋጊዎች ሰዎችን ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእስራኤልንም ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሰሎሞን ልጅ ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳ ቤት ሁሉና ከብንያም ነገድ የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ሰዎች ሰበሰበ። |
ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።
ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑትን ሰዎች ጠቅላላ ድምር ለዳዊት አስታወቀ፤ እነርሱም ከእስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሲሆኑ፥ ከይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ነበሩ፤
በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።”
ንጉሥ አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት ከይሁዳ፥ ታናናሽ ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ሠራዊት ከብንያም ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ በሚገባ የሠለጠኑ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ።