1 ቆሮንቶስ 16:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋራ ነው። አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእኔም ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሁን። አሜን። በኤፌሶን ተጽፎ በጢሞቴዎስና በእስጢፋኖስ፥ በፈርዶናጥስና በአካይቆስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው መጀመሪያዉ መልእክት ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው። አሜን። |
እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል?
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ፥
ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?