1 ቆሮንቶስ 15:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! የምነግራችሁ ይህ ነው፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ እንዲሁም የሚጠፋው ሟች አካል የማይጠፋውን ሕያው አካል አይወርስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ ይህን እንነግራችኋለን፦ ሥጋዊና ደማዊ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም፥ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን አይወርስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም። |
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
ወንድሞች ሆይ! እኔ የምላችሁ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ አጥሮአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለችው ሆኖ ይኑሩ። ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌሉአቸው ሆነው ይኑር።
ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
እንግዲህ እኔ የምለው ይህን ነው፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ ቀደም ብሎ በእግዚአብሔር ተረጋግጦ የተሰጠውን ቃል ኪዳን በመሻር የተስፋውን ቃል ሊያጠፋው አይችልም።