1 ቆሮንቶስ 15:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውርደት የተዘራው በክብር ይነሣል፤ ደካማ ሆኖ የተዘራው ኀይለኛ ሆኖ ይነሣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውርደት ይዘራል፤ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል በኀይል ይነሣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውርደት ይዘራል፤ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፥ በኃይል ይነሣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውርደት ይዘራል፤ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፤ በኀይል ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውርደት ይዘራል፥ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፥ በኃይል ይነሣል፤ |
ያ ራእዩን ያብራራልኝ የነበረው መልአክ እንደገና እንዲህ አለኝ፦ “ሕዝብህን የሚጠብቀው ታላቁ አለቃ ሚካኤል በዚያን ጊዜ ይገለጣል፤ የሰው ዘር ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ ነገር ግን ስማቸው በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈ የአገርህ ሕዝቦች ብቻ በዚያን ጊዜ ይድናሉ፤
እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን።